VPBIMS የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ኮሚሽን ከተማዋን የሚያገለግሉ በጎ ፈቃደኞችን፣ ማኅበራትን እና የአስተዳደር መዋቅሮችን በአንድ ዲጂታል ስርዓት የሚያገናኝበት ኦፊሴላዊ መድረክ ነው።

ንቅናቄዎች
ኮሚሽኑ በመላው አዲስ አበባ የሚያዘጋጃቸው ወቅታዊ የንቅናቄ ንቅናቄዎች።
በአሁኑ ሰዓት የሚታይ ዘመቻ የለም። አዲስ ዘመቻ ሲታተም እዚህ ይታያል።
የኮሚሽነር መልእክት
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣውና እንደገና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 84/2016 ዓ.ም መሰረት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን ይበልጥ ለማዳበርና የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡”
— አቶ ይመር ከበደ - ዋና ኮሚሽነር
በቅርብ ወረዳ ወይም ክፍለ ከተማ ጽሕፈት ቤት በኩል የበጎ ፈቃደኝነት ጥያቄዎን ያስመዘግቡ።
የወረዳ/ክፍለ ከተማ ኃላፊ መረጃዎን መርምሮ ያረጋግጣል፣ ብሔራዊ መታወቂያዎንም ይመለከታል።
ከፍላጎትዎ ጋር ለሚስማሙ ፕሮግራሞችና ማኅበራት ተመድበው ስራ ይጀምራሉ።
ስለ ኮሚሽኑ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የከተማውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የህብረተሰብ ተሳትፎ በዲጂታል ስርዓት ያቀናጃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የከተማው ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ ኮሚሽኑ በማዕከል ፣ በ11 ክፍለ ከተሞችና በ119 ወረዳዎች ተጠሪ ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በ4350 ብሎኮች የህብረተሰቡ ቀጥታ ወኪሎች የሆኑ የካውንስል አመራሮችን ያካተተ መዋቅራዊ አደረጃጀት ዘርግቷል፡፡
ራዕይና ተልእኮ
በ2022 የለማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በጎ ፈቃድን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ የመሠረተ ልማት ፣ የፀጥታ ችግሮችና የበጎ ፈቃድ ተግባራት ፍላጎቶችን በመለየት ፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት ፤ ችግሮች ከምንጫቸው እንዲፈቱ በማድረግ የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
እሴቶች
አሳታፊነት
ሰብዓዊነት
ፍትሐዊነት
ተጠያቂነት
በእውቀትና በእምነት መሥራት
ለለውጥ ዝግጁነት
ጥራትና ወጪ ቆጣቢነት
ችግር ፈቺነት